የኢትዮ-ኤርትራ ውጥረት ወዴት እያመራ ነው?
የኢትዮ-ኤርትራ ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተካረረ ቀጥሎ፤ በአሁኑ ወቀት ከእጅ አዙር ፍትጊያ ወደ ለየለት ጦርነት እየተንደረደረ ይመስላል። ሁለቱም አገራት አንዱ በአንዱ ላይ የተነሱ የነፍጥ አንጋቾችን ትግል በመደገፍ ይወነጃጀላሉ። የቀይ ባህር አፋሮችን ታጣቂ ቡድን የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚደግፍ የኤርትራ መንግስት ወደ አራት ኪሎ የሚጠቁመው የአስመራው መንግስት፤ በአማራ፣ትግራይ እና ኦሮሚያ የሚገኙ ታጣቂዎችን የኢሳያስ መግስት ይደግፋል ሲል ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ጠንካራ ውንጀላ ሲደመጥ እና የቃላት መወራወር በአደባባይ ሲደመጥ ቆይቷል። ባስ ሲልም ደግሞ ኤርትራ ልትወጋኝ የጦርነት ዝግጅት እያደረገች ነው የሚል ግልጽ ደብዳቤም ከኢትዮጵያ በኩል ወደ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ ከውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ቢሮ ተልኮ ነበር።
በኢትዮጵያ በኩል በኤርትራ ላይ በተደጋጋሚ የተወሰዱ ዲፕሎማሲያዊ እርምጃዎች፤ ወደ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ተሸጋግሯል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፤ ለኤርትራው አቻቸው ኦስማን ሳላህ በጻፉት ደብዳቤ ኤርትራ ጦሯን ከተቆጣጠረችው ድንበር በአስቸኳይ እንድታስወጣ አሳስበው አያይዘውም ጦራቸው የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ድንበርን በመጣስ በሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ የሚገኙ አካባቢዎችን ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ አመላክቷል። በተደጋጋሚ ለተመድ የተላኩት ደብዳቤዎች ምላሽ ለማግኘታቸው የታወቀ ነገር ባይኖርም የአሁኑ ደብዳቤ በቀጥታ ለአስመራ መላኩ ግን ያለፉት ደብዳቤዎች በእርግጥም ምላሽ ላለማአግኘታቸው ወይም ደግሞ ተጠባቂ መፍትሄ ሊያመጡ ባለመቻላቸው ነው የሚሉ ሃሳቦች አልታጡም። በዚሁ ደብዳቤ ኤርትራ በሁለቱ አገራት ድንበር ላይ የኢትዮጵያን ግዛት ከመቆጣጠሯ በተጨማሪ፣ በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት የታጠቁ የመንግሥት ተቀናቃኞችን እየደገፈች መሆኑም ተገልጿል።
ኤርትራ ከተቆጣጠረቻቸው ቦታዎች ለቅቃ ከወጣች የኢትዮጵያ መንግሥት በጋራ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ ብሏል። ኤርትራ የቀረቡላትን ጦሯን የማስወጣትና ታጣቂዎችን የመደገፍ እንቅስቃሴ ካቆመች የባሕር በር ጉዳዮችንና በአሰብ ወደብ በኩል የባሕር መዳረሻን ጉዳይ ጨምሮ ሁሉንም የጋራ የጥቅም ጉዳዮችን ለመፍታት በቅን ልቦና ድርድር ለመሳተፍ ፈቃደኛ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግስት በደብዳቤው አስታውቋል። በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የቀረበው ማሳሰቢያ አዘል ጥያቄ በኤርትራ በኩል እስከአሁን የተሰጠ ምላሽ የለም። ከዚህ ቀደም ያለው የኤርትራ አቋም የተቆጣጠረችው የኢትዮጵያ ግዛት እንደሌለና በውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ እንዳልገባች የሚገልጽ ነበር። ይሁን እንጂ ሆርን ፍሪኩዌንሲ ከዚህ ቀደም በነበረው ሳምንታዊ ዝግጅታችን የኤርትራ ወታድሮች ድንበር ጥሰው ወደ ኢትዮጵያ ግዛት እየገቡ መሆኑን መረጃውን ማጋራታችን ይታወሳል።
በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ደግሞ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አስተዳደር ለመቀየር ለሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ከለላ በመስጠት ይከሰሳል። የትጥቅ ትግል አራማጁ የቀይ ባህር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀስ ሲሆን፤ እንደ ብርጌድ ንሓመዱ ያሉ የኢሳያስ ተቃዋሚውች በአዲስ አበባ ቢሮ ከፍተው ይንቀሳቀሳሉ። ዓለም አቀፍ የግጭት ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ክራይስስ ግሩፕ፣ በፈረንጆች 2026 ጦርነት ያስተናግዳሉ ብሎ ከለያቸው 10 አገራት መካከል ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ተካተዋል። በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረው ውጥረት እንደ አሜሪካ ባሉ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ጫና ካልተቀለበሰ፤ አይገመቴ ቀጠናዊ ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል ተቋሙ ማስጠንቀቁ አይዘነጋምየኢትዮ-ኤርትራ ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተካረረ ቀጥሎ፤ በአሁኑ ወቀት ከእጅ አዙር ፍትጊያ ወደ ለየለት ጦርነት እየተንደረደረ ይመስላል። ሁለቱም አገራት አንዱ በአንዱ ላይ የተነሱ የነፍጥ አንጋቾችን ትግል በመደገፍ ይወነጃጀላሉ። የቀይ ባህር አፋሮችን ታጣቂ ቡድን የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚደግፍ የኤርትራ መንግስት ወደ አራት ኪሎ የሚጠቁመው የአስመራው መንግስት፤ በአማራ፣ትግራይ እና ኦሮሚያ የሚገኙ ታጣቂዎችን የኢሳያስ መግስት ይደግፋል ሲል ከኢትዮጵያ መንግስት በኩል ጠንካራ ውንጀላ ሲደመጥ እና የቃላት መወራወር በአደባባይ ሲደመጥ ቆይቷል። ባስ ሲልም ደግሞ ኤርትራ ልትወጋኝ የጦርነት ዝግጅት እያደረገች ነው የሚል ግልጽ ደብዳቤም ከኢትዮጵያ በኩል ወደ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ ከውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ቢሮ ተልኮ ነበር።
በኢትዮጵያ በኩል በኤርትራ ላይ በተደጋጋሚ የተወሰዱ ዲፕሎማሲያዊ እርምጃዎች፤ ወደ ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ተሸጋግሯል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፤ ለኤርትራው አቻቸው ኦስማን ሳላህ በጻፉት ደብዳቤ ኤርትራ ጦሯን ከተቆጣጠረችው ድንበር በአስቸኳይ እንድታስወጣ አሳስበው አያይዘውም ጦራቸው የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ድንበርን በመጣስ በሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ የሚገኙ አካባቢዎችን ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ አመላክቷል። በተደጋጋሚ ለተመድ የተላኩት ደብዳቤዎች ምላሽ ለማግኘታቸው የታወቀ ነገር ባይኖርም የአሁኑ ደብዳቤ በቀጥታ ለአስመራ መላኩ ግን ያለፉት ደብዳቤዎች በእርግጥም ምላሽ ላለማአግኘታቸው ወይም ደግሞ ተጠባቂ መፍትሄ ሊያመጡ ባለመቻላቸው ነው የሚሉ ሃሳቦች አልታጡም። በዚሁ ደብዳቤ ኤርትራ በሁለቱ አገራት ድንበር ላይ የኢትዮጵያን ግዛት ከመቆጣጠሯ በተጨማሪ፣ በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት የታጠቁ የመንግሥት ተቀናቃኞችን እየደገፈች መሆኑም ተገልጿል።
ኤርትራ ከተቆጣጠረቻቸው ቦታዎች ለቅቃ ከወጣች የኢትዮጵያ መንግሥት በጋራ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር ዝግጁ ነኝ ብሏል። ኤርትራ የቀረቡላትን ጦሯን የማስወጣትና ታጣቂዎችን የመደገፍ እንቅስቃሴ ካቆመች የባሕር በር ጉዳዮችንና በአሰብ ወደብ በኩል የባሕር መዳረሻን ጉዳይ ጨምሮ ሁሉንም የጋራ የጥቅም ጉዳዮችን ለመፍታት በቅን ልቦና ድርድር ለመሳተፍ ፈቃደኛ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግስት በደብዳቤው አስታውቋል። በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የቀረበው ማሳሰቢያ አዘል ጥያቄ በኤርትራ በኩል እስከአሁን የተሰጠ ምላሽ የለም። ከዚህ ቀደም ያለው የኤርትራ አቋም የተቆጣጠረችው የኢትዮጵያ ግዛት እንደሌለና በውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ እንዳልገባች የሚገልጽ ነበር። ይሁን እንጂ ሆርን ፍሪኩዌንሲ ከዚህ ቀደም በነበረው ሳምንታዊ ዝግጅታችን የኤርትራ ወታድሮች ድንበር ጥሰው ወደ ኢትዮጵያ ግዛት እየገቡ መሆኑን መረጃውን ማጋራታችን ይታወሳል።
በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ደግሞ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አስተዳደር ለመቀየር ለሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ከለላ በመስጠት ይከሰሳል። የትጥቅ ትግል አራማጁ የቀይ ባህር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀስ ሲሆን፤ እንደ ብርጌድ ንሓመዱ ያሉ የኢሳያስ ተቃዋሚውች በአዲስ አበባ ቢሮ ከፍተው ይንቀሳቀሳሉ። ዓለም አቀፍ የግጭት ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት አድርጎ የሚሰራው ክራይስስ ግሩፕ፣ በፈረንጆች 2026 ጦርነት ያስተናግዳሉ ብሎ ከለያቸው 10 አገራት መካከል ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ተካተዋል። በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረው ውጥረት እንደ አሜሪካ ባሉ አገራት ዲፕሎማሲያዊ ጫና ካልተቀለበሰ፤ አይገመቴ ቀጠናዊ ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል ተቋሙ ማስጠንቀቁ አይዘነጋም።